የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ስልጣንና ተግባር
በሁሉም አስፈፃሚ አካላት፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና ሌሎች የአስተዳደሩ አካላት የስርዓተ ፆታንና ህጻናት ጉዳይ በዕቅዳቸው ላይ ማካተታቸውን ይከታተላል፤ በስርዓተ ፆታ እኩልነት ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ እንዲፈጠር ይደረጋል፤
ሴቶች በክ/ከተማው አስተዳደር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት ይሰራል፤
በክ/ከተማ አስተዳደሩ የሚተገበሩ ህጎች የሴቶች፣ የአረጋዊያን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብትና ደህንነት የሚያስከብሩ መሆናቸውን ይከታተላል፤
የሴቶች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብቶች ስለመጣሳቸው መረጃ ሲደርሰው ከሚመለከተው አካል ጋር ጉዳዩን በማጣራት ውጤቱን ለሚመለከተው የፍትህ አካል ያስተላልፋል፤ ይከታተላል፤
የሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ህጻናት፣ አረጋውያን እና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም የሚያጎለብቱ ትምህርታዊ፣ ሙያዊና የተጨማሪ ክህሎት ሥልጠናዎችን ያዘጋጃል፤ ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
ለሴቶች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናት ፣ጎዳና ተደዳደሪዎች እና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብት፣ ደህንነትና ጥቅም የሚሰሩ ማህበራት እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
ሴቶች፣አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሚመለከት ከልማት ስትራቴጂ አኳያ ተቃኝቶ በወጣ ፕሮጀክት ላይ በክ/ከተማው ውስጥ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ይመሰርታል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
የሴቶች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በሁሉም የጋራ ጥረት መፍትሄ እንዲያገኝ ያስተባብራል፤ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
ለሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኛ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሁሉም የልማት ሥራዎች ውስጥ ፍላጎቶቻቸው እንዲካተት ለማድረግ ከተለያየ ጥቃት መከላከል፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞቻቸው ለማስከበር ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታ የሚሻሻልበትን፤ በማህበራት የሚደራጁበትን እና የብድርና የቁጠባ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ያጠናል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ያደርጋል፤
በየደረጃው ያሉ የሕፃናት አደረጃጀቶችን አቅም በማጎልበት የሕፃናት ተሳትፎ እንዲያድግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፤
የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓትን በማጠናከር የነዋሪዎች ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት እና ዋስትና የሚሻሻሉባቸውና የሚጠበቁባቸው አሰራር ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አቀፍ የተሀድሶ አገልገሎት እንዲታቀፉ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤
በማህበረሰብ አቀፍ ሊታቀፉና ሊደገፉ ያልቻሉ፣ በወንጀል ነክ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ እና ለሱስ ተጋላጭ የሆኑ ህጻናት፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ሰርቶ ለማደር አቅም የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በአስተዳደሩና መንግስታዊ ባልሆኑ ማዕከላት ውስጥ ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
የከፋ የምግብ ችግር ያለባቸው ህጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአዕምሮ ህመምተኞች እና መሰል የህብረተሰብ ክፍሎች ይለያል፣ ይመዘግባል፣ ለምገባ ኤጀንሲ መረጃውን ያስተላልፋል፤
የምገባ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ሁኔታ ክትትል በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲቋቋሙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ የተቋቋሙት ከምገባ ፕሮግራሙ እንዲወጡ ዝርዝራቸውን ለምገባ ኤጀንሲ ያስተላልፋል፤
በተቋሙ ስር ያሉ የቀዳማይ ልጅነት እና የክብካቤ መስጫ ማዕከላትን ያስተዳድራል፤ ያስፋፋል፣ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
በክ/ከተማው አስተዳደር ተቋማት ውስጥ የህጻናት ማቆያ እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
የተለያዩ መንግስታዊ አገልግሎቶችን በነፃ ለማግኘት ለሚጠይቅ ሰው ጥያቄውን አጣርቶ የድህነት ማረጋገጫ ማስረጃ ይሰጣል፤
የማህበራዊ ልማት ፈንድ የሚያስገኝ ፕሮጀክት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
መስራት የማይችሉና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተስብ ክፍሎች በሴፍቲኔት ቀጥታ ድጋፍ ማዕቀፍ ውስጥ ተጠቃሚ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ያስተባብራል፤
በዘላቂ ማረፊያ ቦታ የሚፈፀሙ የባይተዋር ቀብሮችን መረጃ ይይዛል፤ ያጠናቅራል፤ የቀብር ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ በበጎ አድራጎት ማህበር ወይም ድርጅት ውስጥ ቆይተው በሞት የተለዩ እና ሌሎች የባይተዋር ቀብር ያስፈፅማል፤
በክ/ከተማው ውስጥ ያሉ መሠረታዊ እድር እና በየደረጃው የሚገኙት የእድር ምክር ቤቶችን ይመዘግባል፤ ፈቃድ ይሰጣል፤ ባህላዊና ታሪካዊ እሴታቸው ጠብቀው እንዲሄዱ ድጋፍ ያደርጋል፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ያበረታታል፤
የወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ያቋቁማል፤ ይከታተላል፤ ይደግፋል፡