በልደታ ክ/ከተማ የሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ዝርዝር አገልግሎቶች
- 1. ለሴቶች የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ መስጠት፣
- ከፍለው መማር ለማይችሉ ሴቶች የትምህርት እድልና ድጋፍ ማመቻቻት፣
- በጎልማሶች ተግባር ተኮር ትምህርት ማሳተፍ፣
- የነፃ ህክምና ድጋፍ እንዲያገኙ ማመቻቸት፣
- 2. ሴቶችን በገቢ ማስገኛ ዘርፎች እንዲሰማሩ ድጋፍ መስጠት፣
- ተስማሚ ቴክኖሎጅዎችን ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት፣
- በቴክኖሎጅ ሽግግር ዙሪያ የሚከሰቱ ቅሬታዎችን መፍታት፣
- ሴቶች የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ማመቻቸት፣
- 3. ሴቶች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
- የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸት፣
- የቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸት፣
- 4. ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከልና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት፣
- ለጥቃት ተጎጅዎች ተግባራዊ ምላሽ መስጠት፣
- ለሴት የመንግስት ሰራተኞች የትምህርት እድል ማመቻቸት፣
- የህግና የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ ማመቻቸት፣
- 5. አማራጭ የህፃናት ክብካቤ አገልግሎት መስጠት፣
- ጉዲፈቻ አገልግሎት፣
- አደራ ቤተሰብ አገልግሎት፣
- የመልሶ ማቀላቀል አገልግሎት፣
- መልሶ የማዋሀድ አገልግሎት መስጠት፣
- የተቋም አገልግሎት መስጠት፣
- 6. ምክር፣ የምክክርና አመራር አገልግሎት መስጠት፣
- ለህፃናት የስነ ልቦና ምክር አገልግሎት መስጠት፣
- ለህፃናት ቤተሰብ ምክር አገልግሎት መስጠት፣
- 7. የአልሚ ምግቦችን ለእርጉዝ እናቶችና ጨቅላ ህፃናት አቅርቦትና ክትትል፣
- የአልሚ ምግብ አቅርቦት ማመቻቸት፣
- የአልሚ ምግብ አጠቃቀም ላይ ምክር መስጠት፣
- 8. ለህፃናት የቀን ማቆያ ማስፋፋትና ድጋፍ ማድረግ፣
- የማህበረሰብ አቀፍ የህፃናት የቀን ማቆያ ማዕከላት ማቋቋምና መደራጀት፣
- በመንግስት መስሪያ ቤቶች የህፃናት የቀን ማቆያ ማዕከላት እንዲቋቋሙ ድጋፍ ማድረግ፣
- 9. ተጠቃሚዎችን ከመሰረታዊ ማህበራዊ አገልግሎት ማስተሳሰር፣
- ከባንክ ገንዘብ መቀበል የማይችሉ የቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚዎች ውክልና ማመቻቸት፣
- ቅሬታ ማስተናገድ፣
- 10. ለተጠቃሚዎች የኑሮ ማሻሻያ አገልግሎት መስጠት፣
- የጋራና የተናጠል የምክርና አመራር አገልግሎት መስጠት፣
- ወደ ተቋማት የሚገቡ ተቋቋሚዎችን ለተቋማት ማስረከብ፣
- ተቋቋሚዎችን ወደ ቤተሰብ መሸኘት፣፣
- የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ፣
- 11. ለከፋ የማህበራዊ ችግር ውስጥ ለገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ፣
- ለከፋ የምግብ ችግር የተጋለጡ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረገ፣፣
- ተጠቃሚዎችን ከማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረቶች ጋር ማስተሳሰር፣፣
- 12. ለእድሮች የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መስጠት፣
- ለእድር ምክር ቤቶች የፈቃድ እድሳት መስጠት፣፣
- ለእድር ምክር ቤቶች አዲስ ፈቃድ መስጠት፣
- 13. የአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ጉዳይ አካቶ ትግበራን ማስፈጸም፣
- አካል ጉዳተኞች የነፃ ትምህርት እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማመቻቸት፣
- የህግና ምክር ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣
- አምራች አካል ጉዳተኘችና አረጋውያን ለምርቶቻቸው ማሳያና መሸጫ ኤግዚብሽንና ባዛር ማዘጋጀት፣
- 14. ለአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የተሃድሶ አገልግሎት መስጠት፣፣
- የተቋም አገልግሎት መስጠት፣
- የስራ ቅጥር ተጠቃሚ ማድረግ፣
- 15. የሰው ሰራሽ አካልና አካል ድጋፍ አገልግሎት ማመቻቸት፣
- የምክርና አመራር አገልግሎት መስጠት፣
- አቅም ለሌላቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የነፃ ህክምና/ የጤና መደህን አገልግሎት ማመቻቸት፣
- አቅም ለሌላቸው አካል ጉዳተኞች የአካል ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
- አቅም ለሌላቸው አካል ጉዳተኞች የሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ፣
- 16. መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ፕሮጀክቶች ማበልፀግ፣
- 17. የበለፀጉ ፕሮጀክቶችን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
- የፕሮጀክት አማካይ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ፣
- የፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ግምገማ ማካሄድ፣