image
image
image
image
image

አረጋዊያን ለሀገር ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ በማስታወስ በዘላቂነት ውለታቸውን ለመክፈል የሚያስችል አስተሳሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ።

ህዳር 28, 2017
በልደታ ክ/ከተማ "ለአረጋዊያን ደህንነትና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታቸውንን እንወጣ" በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ፤ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ አረጋዊያን እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከበረ። በዚህ የአከባበር በዓል ላይ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጢቂ ድሪባ እንደገለፁት አረጋዊያን ለሀገር ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ በማስታወስ በዘላቂነት ውለታቸውን ለመክፈል የሚያስችል አስተሳሰብ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑ ገልፀዋል። በትውልዶች መካከል ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ አረጋዊያን ጤንነታቸው፣ ደህንነታቸውና ክብራቸው በአግባቡ ከተጠበቀ ጤናማና ተቀባይነት ያለው የትውልድ ሽግግር ሂደት መፍጠር እንደሚቻል ያነሱት አቶ ጢቂ አረጋዊያን መልካም ሲኖራቸው እና ጤንነታቸው ሲጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ መልካም ምሳሌ ይሆናሉ ብለዋል። የልደታ ክ/ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሔለን መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት አረጋዊያን በኢኮናሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ መብታቸው መጠበቅ እንዳለበት አንስተዋል። ወ/ሮ ሔለን አያይዘው አረጋዊያን የጤና፣ የትምህርትና ስልጠና አገልግሎቶችን የማግኘት፤ ምግብ፣ ልብስና መጠለያ የመሳሰሉ መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እና ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ የማግኘት መብቶች እንዳላቸው ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊ አረጋዊያን በበኩላቸው የከተማውና የክ/ከተማው አስተዳደር እያደረገላቸው የሚገኘውን ሁሉ አቀፍ ድጋፍ አመስግነው አዲሱ ትውልድ ለሀገረ መንግስት ግንባታ በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ መሆን እንደሚገባው ከአደራ ጭምር አሳስበዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች