image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት የግማሽ ዓመት የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር አካሄደ

የካቲት 1, 2017
​የልደታ ክፍለ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀምን መሠረት በማድረግ፣ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የሥራ ክፍሎችና ባለሙያዎች የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር አከናውኗል። ​በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን መሀመድ እንደገለጹት፤ ይህ የሽልማት መርሃ-ግብር ከፍተኛ አፈፃፀም ላሳዩ አካላት ተገቢውን ዕውቅና በመስጠት ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ ያለመ ነው። ኃላፊዋ አክለውም፣ የሽልማት መድረኩ በሥራ ሂደቱ ላይ ውጤታማ የሆኑትን ይበልጥ የሚያበረታታ ከመሆኑም በላይ፣ በግማሽ ዓመቱ አፈፃፀማቸው ዝቅተኛ የነበሩ አካላት ክፍተቶቻቸውን በማረም በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ላይ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። በተመሳሳይ በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መቅደስ ያደታ፤ ሴክተሩ በቀዳሚነት የዕውቅና መርሃ-ግብር ማዘጋጀቱን አድንቀዋል። ኃላፊዋ አክለውም የተቋም ግንባታ ውጥናችን ስኬታማ እንዲሆን እንዲህ አይነት የዕውቅናና የማበረታቻ ሥርዓቶች በየጊዜው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል። በዕለቱም ውጤታማ ለሆኑ ባለሙያዎችና ተቋማት የእውቅናና የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች