image
image
image
image
image

"ስለ አባት" አሻራ ቁጥር 4 የተሰኘ የግጥም መድብል በድምቀት ተመረቀ።

የካቲት 14, 2017
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከኦሜጋ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የወንዶችን አጋርነት ለማጠናከር "አሻራ ቁ.4 ስለ አባት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የግጥም መድብል ተመርቋል። በዚህ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሔለን መሐመድ እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ በምትፈልገው የእድገት ደረጃ እንድትደርስና ከድህነት ወጥታ ዜጎቿ የሚኮሩባት እንድትሆን ሴቶች የሚደርስባቸውን ፆታዊ ጥቃት በመከላከልና በማስቆም ልማታዊ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው ይገባል ብለዋል። የሴቶችን መብት ለማስከበር የወንዶች አጋርነት ከምንጊዜው በበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ወ/ሮ ሔለን እንደዚህ አይነት የኪነ ጥበብ ስራዎች ከምንም በላይ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚስተዋለውን የተዛባ የፆታ እኩልነት እሳቤ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም በመድረኩ ላይ ከክ/ከተማው የተውጣጡ ነዋሪዎች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ አርቲስቶች፣ አባት አርበኞች፣ አረጋውያን እና የሃገር ባለውለታዎች በተገኙበት በልዩ ልዩ የመድረክ ዝግጅቶች የግጥም መድብሉ ተመርቋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች