image
image
image
image
image

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ህፃናት ና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኀብረ-ብሔራዊ አንድነት’’ በሚል መሪ ቃል የኢትዮጲያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ተከበረ

ህዳር 22, 2017
በዓሉን የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ያዘጋጀው ሲሆን ፕሮግራሙ በፓናል ውይይት ተከብሯል። በልዩ ልዩ ሁነቶች ሲከበር የቆየውን 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን አስመልክቶ በዴሞክራሲ ግንባታ እንዲሁም በፌደራሊዝም ዙሪያ ልምድ ያላቸው ምሁራንን በመጋበዝ ከ11ዱም ክ/ከተማ ለተወከሉ ለሴቶችና ሴት አረጃጀቶች የተዘጋጀ የማጠቃለያ የፓናል ውይይት መድረክ ተካሂዷል። በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ባስተላለፍት መልዕክት የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በየአመቱ መከበሩ ብሄራዊ አንድነታችን ያከበረ አንዱ ከአንዱ ልምዱን፣ ባህሉንና ተሞክሮውን የሚወስድበት ብሎም የሀገራችን ዜጎች በአንድነት በፍቅር ሀገራዊ ስሜት ተላብሰው የሚያከብሩት ቀን ነው ብለዉ ሴቶችም በየአካባቢያችሁ ከሚገኙ ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ጉርብትናችሁን በማጠናከር በዓሉ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በህብረት ልታከብሩት ይገባል ብለዋል። በበዓሉም የብሄር እኩልነት የሚከበርበት ተዋደን ተፋቅረን እንድንኖር የሚያስችል ቀን በመሆኑ በጋራ ልናከብረውና ሴቶችም ልጆቻችሁን ከስር መሰረታቸው ሀገር ወዳድና ብሄርን ሳይለዩ በአንድነት እንዲኖሩ ማስተማር ይጠበቅባችኋል ብለዋል። የልደታ ክ/ከተማ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሄለን መሀመድ በበኩላቸው በዓሉ ሀገራዊ ስሜት የሚፈጥር ነው ብለው በዓሉ መከበሩ ብሄር ብሄረሰቦች ልምድ እንዲለዋወጡ ያስችላል ሲሉ ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች